“ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” እያሉ ሿሿ አደረጉን

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ የዛሬ 11 ወር በፊት የኢትዬጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነው ሲመረጡ በህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ስለ ይቅርታ፣ ስለ አንድነት እና ስለ መደመር ስለ ኢትዮጵያዊነት ንግግር ሲያደርጉ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ቀደም ተደርጎ በማይታወቅ መልኩ ከጫፍ እስከ ጫፍ በድጋፍ ደስታውን የገለጸው ያለ ምክንያት አይደለም። ሚስጥሩ ላለፉት 27 አመታት ኢትዮጵያዊነት ተዘንግቶ ስለ ዘረኝነት ሲያጠምቁን የኖሩት መሪዎች ተዘንግቶ የነበረው ኢትዮጵያዊነት ስላስታወሱን ነበር።
ዛሬ ግን “ስንወለድ ኢትዮጵያ ስንኖር ኢትዮጵያ ስንሞት ኢትዮጵያዊ” ፤ “ኢትዮዮጵያዊነት ሱስ ነው” ሲሉን ለዳር እስከዳር ያጨበጨብንላቸው ያ ሁሉ ሰበካ ሿሿ እንደሆነ ገና አንድ አመት ሳይሞላቸው የተከናነቡት መጋረጃ ተቀዶ ማንነታቸውን አሳዩን ።የቲም ለማ ቡድን ሁለም የኔ የሚለውን አልጠግብ ባይነት ለማሳካት የሰላም ኮሚቴ ፣የድንበር እና ወሰን ኮሚቴ በማለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቊቊም በይበልጥ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል ያለውን ትኩሳት በመጨመር ሁለቱን ህዝቦች አጣብቂኝ ውስጥ በማስገባት ይህንንም እንደ ጥሩ እድል በመጠቀም ትህነግ ለ27 አመታት እንዳደረገችው ሁሉ አላማውን ለማሳካት ደፋ ቀና እያል ይመስላል። እኛ ኢትዮጵያውያን ተከባብረን በኖርንባት ሀገር አንዱ ቡድን ሌላውን ህዝብ የሚገፋበት እና እኔ ብቻ ልጠቀም የሚለውን የአልጠግብ ባዮች አስተሳሰብ በሚያራምዱ ቡድኖች የሚመራ የአብይ አህመድ መንግስት የገባው ቃል በልቶ ድብቅ ማንነቱን በአጭር ጊዜ በመታየቱ በእነትና ከአንገት በላይ ኢትዩጵያዊነት ሱስ ነው ሰበካ አንሸወድም።

ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር”

Advertisements
Standard

የባንዲራ ፉክክር ፤

ሰንደቅ አላማ ከመስቀል ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተው አለመግባባት አሳፋሪ ነው። ማንኛውም ቡድን አርማውን ማውለብለብ ሀሳቡን የመግለጽ መብት ቢኖረውም ገደብ መኖሩን መርሳት ያለብን አይመስለኝም። ምክንቱም ኦነግም ሆነ ሌላ ቡድን ህንጻዎችን ፣ መንገዶችን የአርማውን ቀለም መቀባት አግባብነት ያለው አይመስለኝም።
ለምሳሌ የኦነግ ደጋፊዎች ይዘውት የወጡት ሰንደቅ አላማ ብዙዎች የተሰዉበት መሆኑ ይታወቃል ታዲያ ብዙዎች የተሰዉበትን ሰንደቅ አላማ የህንጻ መወጣጫ ላይ መቀባቱ በሰምአታት ላይ መቀለድ ይመስላል።

Standard

ተአምረ ኦሮሞ ወአማራ ( ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም) ፐሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

ፍቅሬ ቶሎሳ ራሱን ከማናቸውም የጎሣ ቆዳ ገሽልጦ ወጥቶ፤ መጨረሻውን በቅጡ ሳያውቅ ከሀረር ተነሥቶ በአሜሪካ ዞሮ ኢትዮጵያ ገባ፤ በሁለት እጆቹ ኦሮሞንና አማራን በጋማቸው ይዞ አዛመዳቸው፤ የፍቅሬ ቶሎሳ ሀሳብ፣ እምነት፣ ሕልም (አንዳንዶች ቅዠት ይሉታል፤) ገና ባልታወቀ መለኮታዊ መንገድ ዞሮ ዞሮ ለማና ዓቢይ የሚባሉ ሰዎችን ያፈራ የኢትዮጵያ መሬት ላይ አረፈ፤ የኢትዮጵያን መሬት ከሰሜን እስከደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከምዕራብ ነዘረው፤ ለማና ዓቢይ የሚባሉትን ሁለት ኢትዮጵያውያን ከአንድ መቶ ሚልዮን ሕዝብ መሀል ነቅሶ አውጥቶ አንቀረቀባቸው፤ ለማንና ዓቢይን አንቀርቅቦ አወጣና አንድ አደረጋቸው!
ዘር፣ ፖሊቲካ፣ ጥቅም፣ ሥልጣን፣ ጉልበት ወይም ሀብት አይደለም፤ እግዚአብሔር በረቂቅ ጥበቡ ፍቅሬን ከአሜሪካ ለማንና ዓቢይን እነሱ በማያውቁት መንገድ አገናኝቶ፣ እነሱ ባልገባቸው መንገድ አስማምቶ ሀሳባቸውን ከእውቀታቸው ጋር አዋኅዶ፣ እምነታቸውን ከተግባር ጋር ፈትሎ የኢተዮጵያን ሕዝብ በአዲስ ድርና ማግ እየሸመኑ ኢትዮጵያን የተስፋ አገር እያደረጉ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙሉ ትኩረቱንና ሀሳቡን ከጊዜያዊ ማሸነፍና እልልታ አሳልፎ ከፊቱ በተደነቀሩት ሁለት አቅጣጫዎች አነጻጽሮ መመልከት ያለበት ይመስለኛል፤ አንደኛው፣ በእልልታና በፉከራ እየሰከሩ መጨፈር ሲሆን፣ ሁለተኛው የወደፊቱን ችግርና መከራ፣ ምናልባት ከዚያም አልፎ የጎሣ እልቂትና የማይበርድ የዘር ጥላቻ የፈረካከሰው ማኅበረሰብ ከመፍጠር መታደግ ይሆናል፡፡
በማናቸውም ደረጃ ላይ አሁን ያሉ አመራሮች ትኩረታቸውን ከፈንጠዝያው ወደቀጣዩ መራራ ትግል ቢያዞሩት የኢትዮጵያን ሕዝብ ከአደጋ ከማዳንም አልፈው ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሰው የመሆን ነጻነቶችና መብቶች የተከበሩባት አገርን ለመገንባት፣ በሰው ሳይሆን በሕግ ለሕግ የሚገዙባት አገር፣ ለሁሉም በእኩልነት ከተስተካከለ የኑሮ መተዳደሪያ ሥርዓት ጋር ሊገነቡ የሚችሉ ይመስላል፡፡
እንደገና ኢትዮጵያ የኮሩና የተከበሩ ሰዎች አገር እንድትሆን ከለማና ከዓቢይ ጋር ለትግል መሰለፍ ግዴታ ነው!!!
ሁሉም በአሸናፊነት እንዲኮራ የሚከፍለው ግዴታ ዛሬም ሆነ ነገ፣ በውድም ይሁን በግድ አይቀርም!!!!
ፈንጠዝያን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ለሚመጣው የተሟላ ነጻነት እናቆየው!!!

Standard